አማርኛ
Amharisch Sprache አማርኛ ቋንቋ in Wien Brigittenau በቪየና ብሪጊቴናው VHS የሕዝብ ትምህርት ቤት እንደሚሰጥ ያውቃሉ?
ከ፫ እና ከ፬ ሚሊዮን ዓመት በላይ እድሜ የነበራቸው ሉሲና አርዲ ቋንቋ አልነበራቸውም፣ዘር አልነበራቸውም፣የጎሳ ችግር አልነበራቸውም፣የድንበር ችግር አልነበራቸውም፣ ምክንያቱም እነሱ ሰዎች ስለነበሩ ነው። አቡጊዳቪን
በመጀመሪያ እንኳን ደህና መጡ እያልሁ፣ ይህንን የአቡጊዳቪን ድህረ ገጽ በመጎብኘትዎ በጣም ደስ ይለኛል። የአቡጊዳቪን ዓላማ በቪየና ከተማ ብሎም በኦስትሪያ ውስጥ የትውልድ ቋንቋ አስፈላጊነትን ለማጎላበት የአማርኛም ሆነ የሌሎችንም ቤሔረሰቦች ቋንቋዎች ወጣቱ ትውልድ እንዲያውቅና እንዲገነዘብ የሚያደርጉ ምቹ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት፣ የኢትዮጵያን ባሕል ለማስፋፋትና ለዚህም ራስ ወጥ የሆነ የባሕል ማዕከል ለማቋቋም ነው።
በዚህም ሂደት የኢትዮጵያን ባሕልና ታሪክ ማስተማር፣ የስፖርትና የባሕል ቅርሳቅርሶችን ማስተዋወቅ፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆችን ሁሉ ማሰባሰብና ምግባችንን፣ አለባበሳችንን እንዲያዉቁ ማድረግ የእኛ ብቻ ሳይሆን የማንኛውም ኢትዮጵያዊ መሆን እንዳለበት እናሳስባለን።
የኢትዮጵያ የባሕል ማዕከል አስፈላጊነት ለምን? ኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሰው ዘር የኖረባት፣ ጥንታዊ የሆነችና ታላላቅ ሐይማኖቶችን ያስተናገደች፣ ከሰማንያ በላይ የተለያዩ ቋንቋዎች የሚነገሩባትና፣ ብዙ ብሔሮችና ብሔረሰቦች የሚኖሩባት አገር ናት። በዓለም አቀፍ ደረጃ በስሟ የተጻፉ፣ የተሰባሰቡና ታሪኳን የሚያንጸባርቁ ብዙ መጽሐፍትና ቅርሳቅርሶች በሙዚየሞች፣ በተለያዩ ኢንስቲቲዮቶች፣ በድርጅቶችና በግልሰቦች ዘንድ እንደሚኖር ይታወቃል።
እነዚህ ቅርሶች በተለያዩ ጊዚያት በሚሽነሪዎች፣ በተጓዥ ተመራማሪዎች፣ በዲፕሎማቶች፣ በወራሪዎችና በስጦታ መልክ ከአገር ወጥተው ውጭ አገር እንደሚገኙ የተደበቀ አይደለም። በተለይ በአውሮፓ ውስጥ ባለፉት አርባ ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ በተከሰቱት የሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ችግሮችን ለመቅረፍ ሲባል በጣም ብዙ የአውሮፓ አገሮች መንግስታት፣ በሕዝብና በግለሰቦች አነሳሽነት ከፍተኛ እርዳታ እንዳቀረቡ ይታወቃል። በዚህ ምክንያት የኢትዮጵያን መልክ በገንዘብ ማሰባሰቢያ መልክ፣ የቀረበ እንጂ ደሃ ሕዝብ ሆኖም የራሱ ባሕል፣ ወግ፣ ትምህርትና የትምህርት ማዕከላት ያሉትና የሚኮራ ሕዝብ መሆኑን አሁንም ብዙ አውሮፓውያን አያውቁም። በሌላ በኩል ደግሞ በኢትዮጵያ በደረሱት ችግሮች ምክንያት የአገሪቱ ታሪካዊ እድገት፣ በውስጥዋ ስለሚኖሩት የተለያዩ ቤሔረሰቦችና ማሕበረሰቦች፣ የአገሪቱን ተፈጥሮአዊ መልክዓ ምድርና የተለያዩ ጥንታዊ ቅርሳቅርሶች እንዲሁም፣ እንደሌሎች የሰሜን አፍሪካ አገሮች ቱርዚምን ለመሳብ እንቅፋት የሆኑ የተለያዩ ምክንያታዊ ፕሮፓጋንዳዎችና መፈክሮች አውሮፓን አጥለቅልቀውት ይገኛሉ።
ኢትዮጵያ ከነበረችበት ኋላ ቀርነት አሁንም ያልተላቀቀች ቢሆንም ይህንን ችግር ለመቅረፍ በሌላ መልኩ ለመዘጋጀት ያልቻለችበትን መልኳን፣ ለምሳሌ ጦርነት፣ ርሃብ፣ ድህነት፣ ልመና የመሳሰሉትን መልኳን ለመቀየር እስካሁን የሚደረግ እንቅስቃሴ በአውሮፓ አይታይም።ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ ጊዜያት አገራቸውን እየለቀቁ፣ ለረጅም ጊዜ በተለያዩ ሙያዎች፣ በኤምባሲዎችና በትዳር እንዲሁም በንግድ፣ ከመኖራቸውም በላይ፣ ልጆችን ወልደው አሳድገው የልጅ ልጆቻቸው ማየት የሚቻልበት ወቅት እንደደረስን ስናውቅ፣ እነዚህ ልጆች የመጡበትን የዘር ሐረግ ሳናሳያቸው እንዲያውም ከዚህ ትውልድ እንዳልሆኑ የሚናገሩበትና ለመተውም የሚሞክሩበት ወቅት ላይ እንገኛለን።
ስለሆነም አቡጊዳቪን የኢትዮጵያን የባሕል ማዕከል ለማቋቋም ሲያስብ ብዙ ሁኔታዎችን በማጥናት፣ የትውልድ ቋንቋ አስፈላጊነት፣ የምግብና የአለባበስ ዘይቤያችንን ማስተዋወቅና አገራችን ምንም ርቀን ብንለያትም አሁንም የተወለድንባት እትብታችን የተቀበረባት በመሆንዋ የትም ሆነን ማስታወስ እንድንችል አንድ ማዕከል አስፈላጊ እንደሆነ በማመን በሂደት ላይ እንገኛለን።ለዚህ ለተቀደሰ ዓላም መሳካት የሁላችሁን ትብብር እየጠየቅን የትብብሩ ተካፋይ በመሆናችሁም ከፍተኛ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
ምናልባት ጥያቄም ሆነ አስተያየት ካለዎት አቡጊዳቪን ኤት ጎግል ኮም በሚለው ኢሚል አድራሻችን ይጻፉልን።
ዶር ደስታ ዓለሙ Gefällt mir: Like Wird geladen …
Du muss angemeldet sein, um einen Kommentar zu veröffentlichen.